
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከሩዋንዳ ጋር የገባችበትን ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ለመፍታትና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማስቆም ውይይት እየተካሄደ ነው።
የሁለቱን ሃገራት ተወካዮች እያወያዩ የሚገኙት ደግሞ የቀድሞው የኬኒያ ፕሬዝዳንት ኡህሩ ኬንያ እና የአንጎላው ፕሬዝዳንት ጃኦ ሉሬንሶ መሆናቸው ታውቋል።
በኮንጎ እና በሩዋንዳ ይደገፋሉ በሚባሉት ኤም 23 አምጺ ቡድን መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በማህሌት አማረ
2022-11-14