ሀገሬ ቲቪ

የላቲን አሜሪካ የመጀሪያዋ የኖቤል ተሸላሚ ደራሲ

ላቲን አሜሪካ አሉኝ ከምትላቸው ሴት የስነ ጽሁፍ ባለሞያዎች መካከል አንዷ ናት ። የብዙ ሰወችን ባህሪያት ተንትነው በሚያሳዩ ግጥሞቿ ብሎም ድርሰቶቿ ይቺማ አንድ ሰው ብቻ አይደለችም ይሏታል። ደራሲ ጋብሪኤላ ሚስቱራል ።

ለአንባቢያን ባደረሰቻቸው የስነጽሁፍ ስራዎች ሀገሯ በተለያዩ ጊዜያት ክብርና ሽልማትን ያበረከተችላት ሲሆን በዛሬዋ ዕለት ህዳር 6 / 1945 ዓ.ም ደግሞ ታላቁን የስነጽሁፍ የኖቤል ሽላማት አግኝታለች ።

በ1989 በቺሊ የተወለደችው ጋብሬላ በልጅነት ዕድሜዋ የምትጽፋቸውን ግጥሞች የተመለከተ አንድ የሀገሪቱ ታዋቂ ደራሲ ኤሌጋንስያስ በተሰኘ ታላቅ መጽሔት ላይ እንድትካፈል ጋበዛት ።

ይህ ለኔ ህይወቴን አንድ እርምጃ ከፍ እንዲል ያደረገልኝ አጋጣሚ ነበር ትላለች። ጋብሬላ ሁሌም በመጽሀፎቿ የምታንጸባርቃቸው አወዛጋቢ ሀሳቦችን አንዳንዶች ሲወዱላት አንዳንዶችን ደግሞ የለም ልንቀበለው አንችልም ያስብላቸዋል ።

የቤተሰብ አንድነት ፤ የልጆች አስተዳደግ እንዲሁም ወንድና ሴት ልጆች እኩል መማር አለባቸው የሚሉ ሀሳቦች ሁሌም በድርሰቶቿ ጎልተው የሚታዩ ነበሩ ።

ስራዎቿም በአለማቀፍ ደረጃ ከ20 በሚበልጡ ቋንቋዎች ተተርጉመው ለ አንባቢያን ደርሰዋል። ጋብሬላ ድርሰቶቿን ለአንባቢያን ከማድረስ በተጨማሪ ወደተለያዩ ሀገራቶች በመዞር የትምህርት ስርዐቶች እንዲሻሻሉ የበኩሏን አስተዋጾ አበርክታለች ። በ 3 የአሜሪካ ኮሌጆችም በመምህርነት አገልግላለች ።

ከ1953 ዐ.ም ጀምሮም በኒው ዮርክ የቺሊ አምባሳደር በመሆን ለሀገሯ የሰራች ሲሆን በ በ1957 ዓ.ም በኒው ዮርክ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች ።

ገጣሚ ፤ ደራሲ ፤ እንዲሁም መምህርት ጋብሬላ ሚስቱራል በዛሬዋ ዕለት ላበረከተቻቸው የስነጽሁፍ ስራዎች የኖቤል የስነጽሁፍ ሽልማት ተበርክቶላት ነበርና በ ዕለቱን ከታሪክ እንዲህ አወሳናቹ ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-11-15