እንዲህ እንደኛ በኳስ ፍቅር ሚናውዝ የእግርኳስ ግጥሚያዎችን በአቅራቢያ ይፈልጋል። ታዲያ በርከት ያሉ ቡድኖች ተሰባስበው ለአሸናፊነት ያለ የሌለ ጉልበታቸውን አፍስሰው ይታገላሉ።
ይህ ብርቅ የሆነባት አንዲት ሀገር አስገራሚ ሊግ ባለቤት ነች መባሉን ሰማን እና ልናጋራችሁ ወደድን።
በዓለማችን ላይ ትንሹ ነው የተባለው ሊግ ባለቤቶች በዚያው እግር ኳስ ከመወደድም በላይ በሚፈቀርባት ሀገር እንግሊዝ ነው።
በእንግሊዝ በደቡብ ምዕራብ ኮርንዋል ከ140 በላይ ደሴቶች በአንድላይ የሳይሊ ደሴቶች ተብለው ይጠራሉ።
በእነዚህ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ኳስ ነብሳቸው ነው።
ታዲያ እነዚህ የእግር ኳስ አፍቃሪያን በዛ ባሉ ቡድኖች ለሚደረግ የኳስ ግጥሚያዎች የታደሉ አይደሉም። ባይሆን ግን የራሳችን የሚሏቸው ሁለት ክለቦች ያለመታከት የሚጋጠሙበት ሊግ ባለቤት ናቸው።
ጋሪሰን መድፈኞች እና ዎልፓክ ዋንደርደርስ የክለቦቹ መጠሪያ ነው። ክለቦቹ የውድድር ዓመት ጨዋታዎችን በየሳምንቱ መጨረሻ ላይ እየተገናኙ ያደርጋሉ።
በዓመት ውስጥ ሁለት የዋንጫ ጨዋታዎችን እና እንደባህል የሚደረግ የአዛውንቶች እና የወጣቶች ግጥሚያን በእንግሊዝ የቦክሲንግ ዴይ ጨዋታዎች ሳምንት ላይ ያደርጋሉ።
በዚያው ሀገር ተወልደው ባደጉ ተጫዋቾች የሚደረገው ይህ ሊግ አስገራሚው ነገር ደግሞ ይህ ነው። በሊጉ ተጫዋቾች ለሽያጫይቀርቡም ይልቁንም በዓመቱ የሊጉ ጨዋታ ጅማሮ ላይ የሁለቱ ክለቦች ተጫዋቾች ይቀየጡ እና እዚህ እኛ ጋር በሰፈር ጨዋታዎች እንደሚደረገው ይመዳደባሉ።
ይህ ጨዋታውን የበለጠ ሊጉን ተወዳጅ ለማድረግ የፈጠርነው መላ ነው ባዮች ናቸው። ተጫዋቾቹ እንደየሚጫወቱበት ቦታ በሁለቱ ክለቦች ውስጥ ይመደባሉ። ክለቦቹ የሚጫወቷቸው ጨዋታዎች ድልድልም ቀለል ባለ ሁኔታ ይወጣል።
1893 ዓ.ም. ሊጉ በደሴቶቹ ውስጥ ያሉ ወደ 5 ክለቦች ውስጥ ውድድሩ የሚደረግ ነበር። ከጊዜ ወደ ጊዜ ክለቦቹ እየቀነሱ 1950 ዓ.ም. በኋላ ክለቦቹ ቀንሰው ሁለት ደርሰዋል።
በደሴቲቱ የሚኖሩ እነዚሁ ተጫዎቹ በተለያየ ስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው። ታዲያ በዚህ ያሉ ሁሉም ነገ ሊጋቸው የተሻለ እና ገንዘብ የሚያመጣ ሊግ እንዲሆን ይሻሉ።
አሁን በዚህች ትንሽዬ ሊግ ቮዳፎንን ጨምሮ ሌሎች ስፖንሰር አድራጊዎች ትኩረትን ስባለች። በዚህ ያሉ ታዳጊዎችም ቢሆኑ ከእለተዕለት ተግባራቸው ውጪ እግር ኳስን ዘወትር ይለማመዳሉ። ነገ የተሻለ መሆንን ይሻሉ እና።
በሳምሶን ገድሉ
2022-11-15
