በተያዘው በጀት ዓመት ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
የስራ ዕድል ፈጠራም ከዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቁ ተማሪዎችን ብቻ ታሳቢ ተደርጎ የሚሰራ አለመሆኑንም አብራርተዋል።
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች የ1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት አጠናቀው የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው የሚፈልጉ መሆኑን ጠቅሰው በሁሉም የትምህርት ደረጃ ላሉ ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል መፍጠር ላይ በጋራ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
ስራ መፍጠር ማለት ለችግሮች መፍትሄ መስጠት መሆኑን በመረዳት በየአካባቢው ያሉ ችግሮችን መፍታት ላይ ያተኮሩ የስራ ዕድሎችን ማመቻቸት እንደሚገባም ተናግረዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-11-15
