ሀገሬ ቲቪ

የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ወጣ

ከዚህ ቀደም ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ወጣ፡፡ በአሁኑ እጣ ይወታባቸው ቤቶች በ20/80 18 ሺህ 930 ቤት እና በ40/60 6 ሺህ 843 ቤቶች በድምሩ 25 ሺህ 791 ቤቶች ናቸው ፡፡

ከዚህ በፊት እጣውስጥ ባለመካተታቸው ጥያቄ ሲቀርብባቸው የነበሩ ባለሶስት መኝታ ቤቶች በአሁኑ እጣ ማውጣት ሂደት ውስጥ መካተታቸው ተገልጿል።

በሁለቱም መርሃ ግብሮች በዕጣው የተካተቱ ቆጣቢዎች እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በአግባቡ የቆጠቡ መሆናቸውን ተጠቁሟል፡፡

በብሩክ ያሬድ
2022-11-15