ሀገሬ ቲቪ

የአሜሪካ የሩሲያ የደህንነት ተቋም የስራ ኃላፊዎች በአንካራ ተወያዩ

የአሜሪካ የደህንነት ተቋም ሲአያኤ ዋና ዳይሬክተር ዊሊያም በርንስ ከሩሲያ የውጭ ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ ሰርጌ ናርያሽኪ ጋር በኑክለር ጉዳይ ላይ መከሩ።

ሁለቱ አካላት በቱርክ አንካራ በነበራቸው ውይይት የኒኩለር ጦር መሳርያ አጠቃቀም ላይ ያሉ ልዩነቶች ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

የሰራ ሃላፊዎቹ በአለም ላይ ከኒኩለር ጦር መሳሪያ ጋር ባሉ ስጋቶች ላይ ተወያይተው መፍትሔ አመላክች ሀሳቦች ማስቀመጣቸ ነው የተነገረው።

ውይይቱ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባች በኋላ የተደረገ የመጀመሪያው ነው።

በብሩክ ያሬድ
2022-11-15