ሀገሬ ቲቪ

የቡድን 20 ሃገራት ሰብሰባ ተጀመረ

የአለምን አንድ ሶስተኛ ኢኮኖሚ የያዙት እና ስልሳ ፐርሰርንት የህዝብ ቁጥር ደርሻ ያላቸው የቡድን 20 ሃገራት ጉባኤቸውን ጀምረዋል ። በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደርጉት የኢንዶኔዥያ ፕሬዚዳንት ዮኮ ቪዶዶ ዓለምን ለማዳን ተባብሮ መሥራት ያስፈልጋል ከዚህ ውጭ የሌላ አማራጭ የለንም፣ ሲሉ ተናገረዋል ። ፕሪዘዳቱ የቡድን 20 ሃገራት ጉባኤ ለምጣኔ ኃብታዊ ዕድገት መፈትሄ የሚሰጥ መሆን አለበት ብለዋል ። የጉባኤው ከመጅመሩ አወንታዊ ውጤቶች እንድሚኖሩት ተስፋ የተጣለበት ሆኗል ። ሁለቱ የአለም ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ሃገራት ቻይና እና አሜሪካ ለ 3 ሰአት የፈጀ ሰብሰባን አድርገዋል። የቻይናው ፕሬዝዳን ዥዢፒንግ እና የአሚሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ተገናኝተዋል ። በሰብሰባቸው የተይዋን ጉዳይ አንኳር እንደነበር ተንሰቷል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከሰብሰባው በኋላ “በቻይና በኩል ታይዋንን ለመውረር ምንም ዓይነት የቅርብ ጊዜ እቅድ ያለ አይመስለኝም” ብለዋል፡፡ በስበሰባው ሲጠበቁ የነበሩት የሩሲያ መሪ ቭላድሚር ፑቲን በሰራ በዛት ምክንያት ቀርተዋል ተብሏል ። በምትኩ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌይ ላቭሮቭ ኢንዶኒዢያ ቢደርሱም በልብ ህመም ሆስፒታል ገበተዋል የሚሉ መርጃዎች እንዳሉ ሮይተርስ ዘግቧል ። ሰርጌ ላቭሮቭ ግን ፊት ለፊት ወጥተው እኔ ደህናነኝ የምእራባዊያን ሚዳያዎች ዋሽተዋል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል ። አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስተር ሪሽ ሱናክ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተከሰተ በኋላ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት እና የኑሮ ውድነት እየጨመረ መሄዱን ለማስወገድ የተቀናጀ እርምጃ እንዲወሰድ ቡድን 20 ሃገራትን እንደሚጠይቁ ገልጸዋል። በተጨማሪም ሱናክ የቡድን 20 ሃገራት መሪዎች ለዩክሬን ድጋፍ እና አንድነታቸውን ማሳየት ይገባል ብልዋል ። የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚሼል በበኩላቸው ሰኞ ምሽት በፅሁፍ በላኩት መልዕክት ላይ የቡድን 20 ሃገራት መሪዎች የኑክሌር መሣሪያዎችን መጠቀምን ወይም የኒውክሌር ስጋት ለማሰወገድ በባለስልጣናት መካከል ስምምነት ያለ ቢመስለም መሪዎቹ በተግባር ማረጋገጥ ይገባቸዋል ብለዋል። በጉባኤው ለአለም የሚበጅ ውሳኔዎች ይወሰናሉ ቢባሉም የዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት ላይ ሃገራት ያላቸው የተለያየ አቋም ጉባኤው ውጤታማ እንዳይሆን ያደርጋል የሚል ስጋት አለ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-15