ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቋሙ።
ሙስና ዛሬ የሀገራችን የደኅንነት ሥጋት ሆኗል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ብልጽግና የምናደርገውን ጉዞ እግር ቶርች አሥሮ ለመያዝ ከጠላቶቻች እኩል ሙሰኛው እየታገለን ነው ብለዋል።
አይነት እና ይዘቱን እየቀያየረ ለሀገር ሳንካ የሆነውን ሙስና በህግ ብቻ መከላከል ስለማይቻል 7 አባላት ያሉት የፀረ-ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ዶ/ር ጌዴዎን ጢሞቴዎስ፣ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ፣ አቶ ሰሎሞን ሶቃ፣ አቶ ደበሌ ቃበታ፣ ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እና አቶ አብዱሃሚድ መሃመድ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት ተደርገው መመረጣቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-11-17
