ከኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ የተዘረጋው እና አምስት መቶ ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ የወጣበት ባለ 500 ኪሎ ቮሌት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያ ዛሬ በይፋ የኤላክትሪክ ሽያጭ ጀምሯል።
ይህ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ማስተላልፊያ መስመር ከኬኒያ ባሻገር ከታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ላሉት ሀገራት እስከ ሁለት ሺህ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ አቅም ያለው እንደሆነ ተገልጿል።
ኢትዮጲያ ወደ ኬኒያ በምትልከው የኤሌክትሪክ ሃይል ብቻ በአመት እስከ አንድ መቶ ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንድታገኝ ያስችላታል ሲል የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል።
በማህሌት አማረ
2022-11-17
