ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ ወሮታዋን አሳደገች

አሜሪካ የአልሸባብ መሪዎችን ለጠቆመኝ የምሰጠውን ወሮታ 10 ሚሊዮን ዶላር አድርሻለው አለች።

በሱማሊያ የሚንቀሳቀሰውን አሸባሪ ቡድን መሪዎች እና ከአልቃይዳ ጋር የሚደረግ የፋይናንስ ፅርን የሚመለከት ሁነኛ መረጃ ለሚያበብላት የምትሰጠውን ወሮታ በእጥፍ ማሳደጓን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የሀሰን ሼክ መሀሙድ መንግስት በቡድኑ ላይ የተከፈተውን ሰፊ ጥቃት ተከትሎ አሸባሪው ቡድን አልሸባብ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ሳይቀር የሽብር ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል።

አሜሪካም የአልሸባብን መሪ “አሚር” አህመድ ዲሪዬ፣ ሁለተኛ አዛዥ የሆነውን ማሃድ ካራቴ እና ጄሃድ ሙስፋፋን ጨምሮ በቡድኑ የተለያየ ሚና ያላቸው የአሜሪካ ዜጋ የሆኑ አሸባሪዎችን ለጠቆመኝ ለእያንዳንዳቸው 10 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ ለመክፈል ተዘጋጅቻለው ብላለች።

በሳምሶን ገድሉ
2022-11-17