ሀገሬ ቲቪ

አርጤም አንድ ወደ ጨረቃ መጠቀች

የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ የሰው ልጅን ወደ ጨረቃ ለመላክ የሚያደርገው ሙከራ አካል የሆነችው አርጤም የተሰኘችው መንኩራኩር ትናንት መጥቃለች።

አፖሎ የተሰኘው የወደ ጨረቃ የሚደረግ የምርምር ጉዞ ካበቃ ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ጨረቃን የመርገጥ ጉዞ አርጤምስን በማምጠቅ አንድ ብሏል።

ከምድር ከ2 ሚሊዮን ኪሎሜትሮች በላይ እርቃ ጨረቃ ላይ ምህዋሯን የምዘረጋው መንኩራኩሯ ለ25 ቀናት የሚቆይ ተልዕኮን ትወጣለች።

ከጨረቃ 100 ኪሎ ሜትሮች ዕርቃ ጨረቃን በመዞር በጥልቁ ጠፈር ውስጥ ለሚደረገው ምርምር የሚሆኑ ሙከራዎችን ታደርጋለች ተብሎም ይጠበቃል።

መረጃውን ከናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ገጽ ላይ አግኝተነዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-11-17