ሀገሬ ቲቪ

ኮቪድ 19 መከሰቱ የታወቀበት ዕለት

የኮሮና ቫይረስ ከ6.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ሰዎ ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል። በቻይና ሁቤ ግዛት የ55 ዕድሜ ያላቸው ግለሰብ በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀው ከሁለት ዓመት በፊት በዛሬዋ ዕለት ነበር።

ይህም የኾነው የሕክምና ባለሙያዎች ቫይረሱን በቻይና ዉሀን ግዛት መከሰቱን ይፋ ከማድረጋቸው ከአንድ ወር በፊት እንደኾነ የሳውዝ ቻይና ሞርኒግ ዘገባ ያሳያል። በወቅቱ ቫይረሱ ከአንድ የእንሳ ተዋጽኦ መሸጫ ገበያ ተነስቷል የሚል እስካሁን ድረስ የዘለቀ ጥርጣሬ አለ።

ከሁለት ዓመት በፊት በቻይና እንደተከሰተ ይፋ የኾነው ኮቪድ19 ከቻይና አልፎ ወደ ሌሎች ሀገራት ለመዛመት ያን ያህል ጊዜ አልፈጀበትም።

ቫይረሱን ለመከላከል ሀገራት ድንበራቸውን ቢዘጉ የአውሮፕላን በረራዎን ቢሰርዙ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ቢጥሉም ቫየረሱን ግን ሊከላከሉት አልቻሉም። 288 ሀገራት እና ገዛቶች አሁን ላይ ቫይረሱ እንደሚገኝባቸው ወርልዶ ሜትር ላይ የሰፈረው መረጃ ያሳያል።

እንደ ንክኪ ባሉ ቀላል መንገዶች የሚተአለፍ ቫይረስ በመኾኑ የሥርጭት አድማሱን ጨምሮታል። ይህ ቫይረስ ከምን እና እንዴት መጣ የሚለውን ከይኾናል ውጪ እርግጠኛውን መናገር አልተቻለም ሳይንቲስቶች ቫይረሱ ከእንሣዎች በተለይም ከለሊት ወፍ እና ወይ ደግሞ ፓንጎሊን ከምትባል በአፍሪካና ኤሺያ የምትገኝ ኤሊ መሳይ እንስሣ ወደ ሰው ተላልፎ ሊኾን ይችላል የሚል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ቫይረሱ ከተከሰተ በኋላ በበርካታ ሀገራት ዜጎች ለከፋ ሕመም እና ሞት ተዳርገዋል። አሜሪካ ደግሞ ከ1.1 ሚሊየን በላይ ዜጎችን በማጣት ቀዳሚዋ ናት።

አሜሪካን ጨምሮ የዓለም ቀልብ ቫይረሱን ሊመክት የሚችል ክትባት ማምረት ላይ ኾነ ። ዓለም አቀፍ ተቋማትም ትኩረታቸውን በዚህ ላይ አደረጉ። የዓለም ምጣኔ ሀብት ክፉኛ ተጎዳ። ኢንዱስትሪዎች ሥራቸውን በማቆማቸው ሠራተኞቻቸውን ለመቀነስ ተገደዱ።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የዓለም ምጣኔ ሀብት ላይ ከፈተኛ ጉዳት ያደረሰ ቫይረስ ኾነ። ቫይረሱ ከተከሰተ ከዓመት በኋላ 5.2 % የምጣኔ ሀብት ውድቀት የሚጠበቅ እንደነበር የዓለም ባንክ ማሳወቁ የሚታወስ ነው።

የግዙፍ ምጣኔ ሀብት ባለቤት እና የቫይረሱ መነሾ እንደኾነች የሚነገርላት ቻይና የዜሮ ኾቪድ ፖሊሲን አውጥታ እስካሬ ድረስ ተግባራዊ ማድረጓ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ አክብዶታል። እንደ አፍሪካ ባሉ አነስተኛ ገቢ ባሉባቸው ሀገራት ቫይረሱ በሰው ሕይወት ኾነ በምጣኔ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

ቀስ በቀስ በተለይም ቫይረሱ በሰዎች ሕይወት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይችላሉ የተባሉ ክትባቶች መመረት ከጀመሩ ወዲህ የቁጥጥር እርምጃዎች ሙሉ ለሙሉ እየተተው መጥተዋል ሀገራትም ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴአቸው ተመልሰዋል በኛም ሀገር ቫየረሱ ከ7500 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ቀጥፏል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-17