ሀገሬ ቲቪ

አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ይሆናል

አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በ2016 ዓ.ም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በተያዘው ዓመት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መስጠት እንደሚጀመር ገልጿል። 31ኛው አገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄድ ነው።

በጉባኤ እንደተገለጸው በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን የትምህርት ጥራት ችግር ለመቅረፍ እና በቀጣዮቹ 5 ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የለውጥ ሥራዎች ይሰራሉ ።

በብሩክ ያሬድ
2022-11-18