
የናይጀሪያ መንግሥት በሀገሪቱ በጣም ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው እና በ1.5 ቢሊየን ዶላር ወጪ የተገነባው ወደብ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን አስታውቋል።
በናይጀሪያ ትልቁ የሆነው የሊኬ ወደብ ዘጠና ሄክታር ስፋት ያለው ሲሆን በዓመት 2.7 ሚሊዮን 20 ጫማ ርዝመት ያላቸው ኮንቲነሮችን ማስተናገድ ይችላል ተብሏል።
የዚህ ወደብ መገንባት የሃገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ከማቀላጠፍ ባሻገር ለቀጠናውም ትልቅ እፎይታን ይሰጣል መባሉን ሲኤን ኤን ዘገቧል።
በማህሌት አማረ
2022-11-18