ሀገሬ ቲቪ

የኤዥያን ፓስፊክ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ ተጀመረ

የኤዥያን ፓስፊክ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ በታይላንዷ ባንኮክ ተጀምሯል። በዋጋ ግሽበት፣ በጂኦ ፖለቲካዊ ውጥረት እና በወረርሽኝ ምክንያት የመቀነስ አደጋ ያንዣበበትን የቀጠናው ሀገራት የኢኮኖሚ ለማንሰራራት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ይመክራል ተብሏል።

በጉብኤው የተገኙት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ሺንፒንግ ግዜው ተደጋገፈን ካጋጠመን ችግር የምንወጣበት እንጂ የምንፎካከርበት አይደለም ብለዋል።

ጉባኤው ለቀጠናው የደህንነት ስጋት እየሆነች ባለችው ሰሜን ኮርያ ጉዳይ ላይም ተውያይቶ ወሳኔ ያሳልፋል መባሉን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

በማህሌት አማረ
2022-11-18