የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እና የሱዳን ጠቅላላ የደህንነት አገልግሎት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከሱዳኑ አቻቸው አህመድ ኢብራሂም አሊ ሙፍዲል ጋር በካርቱም መክረዋል።
ሁለቱ የኢትዮጵያ እና ሱዳን የመረጃ እና ደህንነት ተቋማት ተሞክሮ እና መረጃ ለመለዋወጥ፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት፣ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን ለመከላከል እና የሁለቱን ሀገራት ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-11-21
