ሀገሬ ቲቪ

የህዳር በሽታ እና ህዳር ሲታጠን

በኢትዮጲያ ከ 40ሺ በላይ ዜጎችን ህይወት ነጥቋል የህዳር በሽታ።በሽታውን ለመከልከለም ሲወሰዱ ከነበሩ ርምጃዎች ወስጥ ደግሞ የአከባቢ ጸዳት ዋነኛው ነበር።

ይህ ተግባር ቀጥሎ ታዲያ ዛሬም ደረስ ህዳር 12 ‘ህዳር ሲታጠን’ እየተባለ ይከወናል። የዛሬው እለቱን ከታሪክ ትኩረት ነው።

በሀገራችን ከተከሰቱ ወረርሽኞች አንዱ ነው። ይሄው ክስተት ወደ 1911 ዓ.ም. ይመልሰናል። በዚሁ ዓመት ከህዳር 7 እስከ ህዳር 20 የተከሰተ በሽታ ነው፤ የህዳር በሽታ።

በነዚያ ጊዜያት ታዲያ 40 ሺህ ያክል ሰዎችን መግደሉ የነገራል። በሸታው በአለማችን ደረጃ ። ስፓኒስሽ ፍሉ ወይንም ኢንፉሊንዛ በመባል ይታወቃል ።

ከወደ ስፔን መነሻወ እንዳደረግ ቢነገርም ለመጀመሪያ ጊዜ በምርመራ የተገኘው በአሜሪካ ካንሳስ በሚገኘው ፉንስተን የወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ነው።

በሽታው አንድ ሶስተኛ የሚሆነውን የአለም ህዝብ አጥቀቷል ።ከ50 ሚሊየን በላይ ስዎችችን ደግሞ ወደ ሞት መርቷል ።

በኢትዮጵያም ቢሆን ይህ በሽታ በ1911 ዓ/ም ከኅዳር 7 እስከ 20 ቆየቷል። ኅዳር 12 ቀን ደግሞ በበሸታው ከበፊቱ ቀናት የሚበልጥ ሰዎች እንዲሞቱ እና በህመም እንዲወደቁ አደርጓል ፡፡ በሽታው እንደ ጉንፉን ሆኖ በሳል ይጀመር እና ከዚያም ነስር፣ መቀጠልም ራስን በማሳት ለሞት ያደርሳል፡፡

በወቅቱ በአዲስ አበባ በቀን ከ300 በላይ ሰው በዚህ በሽታ ይሞት ነበር። በአጠቃላይ በአዲስ አበበ ብቻ በሸታው ከ9000 በላይ ዜጎችን ህይወት ያስጣ ሲሆን በሃሪቱ በአጠቃላይ ከ 40ሺ በላይ ዜጎችን ህይወትን ነጠቋል ።

የህዳር በሽታ በኢትዮጵያ በቆየበት ጥቂት ቀናት መጥፎ ትዝታን ጥሏል ። በዚያ ሰሞን መቃብር የሚቆፍር፤ ሬሳ ተሸክሞ የሚወስድ ሰው ማግኘት የማይታሰብ ሆኖ ህዝቡ ተቸግሮ ነበር። አባት የልጁን ሬሳ ሳይቀር ራሱ ተሽኮሞ ወስዶ ለመቀበር ተገደደበትም ሁኔታወች ነበሩ ፡፡

ይህም በሃሪቱ ክፉ ቀናት ከሚባሉ አንዱ ሆነ በሽታው ቤተመንግሥትም ዘልቆ አልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪና ባለቤታቸው ልዕልት መነን እንዲሁም ንግሥት ዘውዲቱም ተይዘው ነበር፡፡

በመጨረሻም በሽታው በቀላሉ ሊስፋፋ የሚችለው ከጽዳት ጉድለት የተነሳ መሆኑ ስለታወቀ ሁሉም ህዝብ በየአካባቢው የሚገኘውን ቆሻሻ እያሰባሰበ እንዲያቀጣል ተደረገ ።ይህም ልማድ በየዓመቱ ቀጥሎ ህዳር 12 በመጣ ቁጥር "ህዳር ሲታጠን" እየተባለ እዚህ ደርሷል ፡፡

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-21