ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በደብረብርሀን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ችግር ውስጥ ነን አሉ። ተፈናቃዮቹ ከወለጋ ዞን ተፈናቅለው በደብረብርሀን ከተማ የሚገኙ ናቸው። ከተፈናቃይ ጣቢያዎች አንዱ ደግሞ ቻይና ካምፕ የተባለው ይገኛል።
ጣቢያችን ያነጋገራቸው በዚህ የሚኖሩ ተፈናቃዮች የምግብ እንዲሁም የአልባሳት ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል።
በተለያዩ የድጋፍ ተቋማት እና የመንግሥት ድጋፍ መሠረታዊ አቅርቦቶች እየቀረቡ ቢሆንም ካለው የተፈናቃይ ቁጥር ጋር የማይመጣጠን እና የሚያንስ ነው ብለዋናል።
ለመተኛትም ቢሆን በጣም በተጨናነቀ ድንኳን ውስጥ በርካታ ተፈናቅይ ዜጋ ስለሚገኝ አመቺ አልሆነም ሲሉ ገልጸዋል።
በሀገራችን በግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ በርካታ ዜጎች እንዳሉ ይታወቃል።
ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው እና በደብርብርሃን ከተማ በሶስት የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ከ25 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ።
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-21
