ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ ያለ አገልግሎት የተቀመጠ የ90 ሄክታር መሬት ውል ተቋረጠ

በአዲስ አበባ ከተማ ለረዥም ጊዜ ያለ አገልግሎት ታጥሮ የቆዬ የ90 ሄክታር መሬት ውል መቋረጡ ተገለጸ።

ይህንን መሬት ተቋማት እና ግለሰቦች ያለ አገልግሎት አጥረው ያቆዩት የነበረ ሲሆን የከተማዋ መሬት እና ልማት አስተዳደር ቢሮ ውሉ እንዲቋረጥ ማድረጉን አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ቀንዓ ያደታ ውላቸው ከተቋረጡት መካከል ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ መሬት ወስደው ያላለሙ እንደሚገኙበትም ጠቁመዋል።

እነዚህ መሬቶች በቀጣይ በግልጽ ጨረታ ለአልሚዎች ይተላለፋሉ ብለዋል። ዶ/ር ቀንዓ በአዲስ አበባ በመሬት አስተዳደር ላይ ያሉትን የሌብነትና የመሬት ወረራ ችግሮችን መፍትሄ ለመስጠትም አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-11-21