ሀገሬ ቲቪ

የኑሮ ውድነት የምስራቅ አፍሪካን ኢኮኖሚ እየፈተነው መሆኑ ተገለጸ

የምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ ባሻቀበው የኑሮ ውድነት እየተፈተነ መሆኑ ተገለጸ። የቀጠናው ኢኮኖሚ ከ ዘጠኝ በመቶ እስከ ሁለት እጥፍ በሚደርስ የዋጋ ንረት እየተፈተነ ነው ሲል ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል።

የዩኤንን መረጃ ዋቢ እንዳደረገው የርዋንዳ የዋጋ ንረት ከባለፈው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ አሻቅቧል። ዝቅተኛ የሚባለው የኬንያ አሁናዊ የዋጋ ንረት ደግሞ 9 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል።

የቀጠናው የኢኮኖሚ ዘርፉ ኃላፊዎች ወቅታዊ በሆነው የዋጋ ንረት እና ያሻቀበውን የኃይል እና የምግብ ዋጋ መቋቋም የሚያስችል ፖሊሲን መቅረጽ ይጠበቅባቸዋል ሲልም ዘግቧል።

በአብርሃም በለጠ
2022-11-21