የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩስያ በዩክሬይን ቁጥጥር ስር ባለው የኒውክሌር ማብላያ ዛፖርዥያ እያደረገች ያለውን ጥቃት እንድታቆም ጠየቀ።
በአውሮፓ ትልቁ የኒውክሌር ማብላያው በዛፖርዥያ ደርሰበት በተባለው ጥቃት አካባቢውን ፍንዳታ አናውጦታል ተብሏል።
የዩኤን የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ኃላፊ እብደት ያሉትን ይሄንንው አካባቢውን ዒላማ ያደረገ ያሉትን የሩስያን ጥቃት አውግዘዋል።
የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጄንሲም ቢሆን በመግለጫው በኒውክሌር ማብላያው የሚደርስ ማንኛውም ፍንዳታ ተቀባይነት የለውም ብሏል። ሩስያ በበኩሏ በምስራቅ ዩክሬይን የምታደርገውን ጥቃት አጠናክራለች።
በአብርሃም በለጠ
2022-11-21
