ሀገሬ ቲቪ

የሰሜኑ ጦርነት በአፍሪካ ቀንድ ላይ አሉታዊ ተጸዕአኖ አሳድሯል ተባለ

ሱዳን እና ኤርትራ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ጦርነት በቀጥታና በተዘዋዋሪ የራሳቸው ሚና እንደነበራቸው ተነገረ። በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ናቸው ይህንን የተናገሩት።

ምን ዓይነት ሚና ነበራቸው የሚለውን ግን በግልጽ አላብራሩም። ይሁን እንጂ ጦርነቱ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ላይ ማኀበራዊ አኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ አሳድሯል ብለዋል።

የሰሜኑ ጦርነት ብቻ ከ600 ሺህ ያላነሱ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል ተብሎ እንደሚገመትም ኦባሳንጆ ተናግረዋል። በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለይም በአፋር፣ በአማራና በኦሮሚያ የደረሰው ሞት ቢጨመር ቁጥሩ ወደ አንድ ሚሊየን ይጠጋል ብለዋል።

ከዚያ ባለፈ ኢትዮጵያ በጦርነቱ የወደመውን መሠረተ ልማት መልሶ ለመገንባት 25 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ሲሉ ሴማፎር ለተሰኘ መጽሔት ተናግረዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-22