ሀገሬ ቲቪ

በሌ/ኮ አብዲሳ አጋ የተሰየመ ት/ቤት እና ሃውልት ተመረቀ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክ/ከተማ የተገነባው እና በሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ስም የተሰየመው የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና ሃውልት የሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ቤተሰቦች፣ የጀግ ኖች አርበኞች ማህበር አባላት እና ሌሎች የክብር እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ ሉሌ ትምህርት ቤቱ ከ1965 ዓም ጀምሮ እገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ገልጸዋል።

አሁን ግን የፈራረሰው ሕንጻ ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ ለማድረግ መልሶ እንዲገነባ ተደርጎ ለምርቃት መብቃቱን ተነግረዋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ት/ቤቱን ወደ ሁለተኛ ደረጃ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚያሳድገው ቃል መግባታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በማህሌት አማረ
2022-11-22