
ከአልጄሪያ አልጀርስ ተነስቶ ናይጄሪያ ሌጎስ የሚደርሰው መንገድ ግንባታ ወደ መገባደዱ ተቃርቧል ተባለ።
ከ 50 ዓመታት በፊት የተወጠነው ይሄው አፍሪካን በመንገድ እና በኢንተርኔት የማስተሳሰር ውጥን ወደ መገባደጃው ተቃርቧል።
5 ሺሕ ኪሎሜትሮችን የሚሸፍነው መንገዱ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ኒጀር፣ ማሊ፣ ቻድ እና ናይጄሪያን ያገናኛቸዋል ተብሏል።መንገዱ እና የኢንተርኔት ዝርጋታው ሀገራቱን በኢኮኖሚ ከፍ እንዲሉ እና የተሻለ ፍጥነት ያለው ኢንተርኔትን እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል።
የመንገዱን ረዥሙን ክፍል የሚይዘው በአልጄሪያ በኩል ያለው መንገድ ከኒጀር ድንበር ደርሷል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-11-22