
የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ወደ እስር እንዲመለሱ የሀገሪቱ የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ፍ/ቤት ውሳኔ ሰጠ።
ከ 2002 እስከ 2011 ዓ.ም በነበረው የሥልጣን ዘመናቸው በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ጃኮብ ዙማ ችሎት በመድፈር በቀረበባቸው ክስ 15 ወር ወይም የአንድ ዓመት ከሦስት ወር ታስረው ነበር።
በጤና መታወክ ሳቢያ ለሕክምና ክትትል ተብሎ ከእስር እንዲለቀቁ ተደርጎም ነበር። የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ታዲያ ወደ ወኀኒ እንዲመለሱ ውሳኔ ማስተላለፉን አፍሪካን ኒውስ አስነብቧል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-22