"ኢትዮጵያ ታምርት" የተሰኘው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው ይህ የተባለው። የኢንዱስትሪ ሚንስቴር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሺሰማ ገ/ሥላሴ እንደተናገሩት ከሆነ በሀገሪቱ ያሉ ኢንዱስትሪዎች በፋይናንስ ነክ ጉዳዮች፣ በግብዓት ዕጥረት እና በተለያዩ ምክንያቶች የህልውና አደጋ ተጋርጦባቸዋል። በደብረብርሀን እንዲሁም በአዳማ አካባቢ ሰራተኛ መልምለው እና ማሽን ተክለው በመሰረተ ልማት አለመሟላት ምክንያት ሥራ መጀመር ያልቻሉ እንዲስትሪዎች መኖራቸውንም ጨምረው ገልጸዋል። በዚህም ሳቢያ አሁን ላይ በአምስት ክልሎች 390 ኢንዱስትሪዎች ተዘግተዋል ብለዋል ኃላፊው። በትግራይ እና በሌሎች ክልልሎች የተዘጉ ኢንዱስትሪዎች ቢጨመሩ ደግሞ ቁጥሩ ከዚህ እንደሚልቅ ነው ዴኤታው የተናገሩት። በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን የተነገረው "ኢትዮጵያ ታምርት" የተሰኘው ንቅናቄ ታዲያ በነዚህ ኢንዱስትሪዎች የሚታዩ ተግዳሮቶችን እንደሚፈታ ነው የተጠቆመው።
በሀገሬ ቲቪ
2022-04-27
