ሀገሬ ቲቪ

በኢንዶኔዢያ በመሬት መንቀጥቀጥ 167 ሰዎች ሞቱ

በኢንዶኔዢያ ጃቫ በተሰኘች ደሴት 5ነጥብ6 ማግኒቲውድ በተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ 167 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ። ከ 700 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በሕንፃ ፈርስራሽ ተቀብረው ያልተገኙ ሰዎች እንዳሉ ፍራንስ 24 ዘግቧል። በአደጋው ከ 2ሺህ በላይ ቤቶች መውደማቸውን የኢንዶኔዢያ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ አስታውቋል።

ከ5 ሺ በላይ ሰዎን ደግሞ አደጋው ከተከሰተበት ቦታ ማንሳት ተችሏል። ምን አልባትም የሟቾች እና የተጎጂ ሰዎች ቁጥል ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ተጠቁሟል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-22