በዓለማችን ላይ 970 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በአዕምሮ ጤና ችግር እንደሚሰቃዩ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።
ይህም ከአራት ሰዎች ውስጥ አንዱ በህይወቱ ጉዞ ውስጥ የሆነ ግዜ ላይ ለአዕምሮ ጤና ችግር እንደሚጋለጥ ይጠቁማል።
በመላው ዓለም ከሚኖረው ሕዝብ ውስጥ ከ14 በመቶ በላይ የሚሆነው በዚሁ የአዕምሮ ጤና ምክንያት ለሞት ይዳረጋል።
በሀገራችን ኢትዮጵያም ቢሆን የአዕምሮ ጤና እምብዛም ትኩረት የማያገኝ፤ ነገር ግን ይህን ያህል ነው በማይባል ደረጃ የዚህ ህመም ተጠቂው ብዙ ነው ።
በዚህ ህመም ላይ የማህበረሰቡን አተያይ በተመለከተ የጠየቅናቸው የስነ ልቦና ባለሙያው አቶ ኖህ ውብሸት ይህንን ይላሉ።
የአዕምሮ ህመም በባህሪው ለእኛ የተለመደ የሚመስለን እና የማናስተውለው መሆናቸው ህመሙን ወሰብሰብ እንዲል እንዳረገው ባለሙያዎች ይናገራሉ።
እንደእኛ በአብሮነት መኖርን ለታደለ ማህበረሰብ ደግሞ የህመሞቹን ባህርያት ማወቁ ጠቃሚ ነው።
ከ400 የሚልቁት እነዚሁ የአዕምሮ ህመሞች እንደየ ደረጃቸው የሚለያዩ ሲሆኑ ይህንን ህመም ለመረዳት ልናውቃቸው ይገባል ያሉንን ባለሙያው ጠቁመውናል።
እራሳችንን ከአዕምሮ ጤና ችግር ለመከላከል ሻገር ሲልም ተከስቶ ከሆነም ለማከም መደረግ አለባቸው ያሉንን ባለሙያው እንዲህ ይነግሩናል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-11-22
