በአለም የኢኮኖሚ ሰርአት ወስጥ በዘርፉ የሰለጠን እና ወጣት የሆነ የሰው ሃይል አስፈላጊነቱ ግልጽ ነው። ሃገራት የሚገጥማቸውን የሰው ሃይል እጥረት ከሌሎች ሃገራት ዜጎችን በመቀበል ሊደርሱ የሚፈለጉበትን የኢኮኖሚ እድገት ያሳካሉ ።
ካናዳ በዚሁ መንገድ ያለባትን የሰው ሃይል ችግር ለመቀረፍ እየሰራች ትገኛለች ። በቅርቡ በወጣ መረጃ የካናዳ መንግስት ወደ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞችን እስከ 2025 የመቀበል እቅድ እንዳለው ይፋ አደርጓል ።
ይህም ማለት በየአመቱ ወደ አምስት መቶ ሺ የሚጠጉ ሰደተኞች ወደ ካናዳ ይገባሉ ማለት ነው ። ካናዳ ሰደተኛን ለመቀበል ያሳየቸው ፍላጎት ከአሜሪካ እና ከ እንግሊዝ ሲነጻጸር በአራት እጥፍ ከፍ ያለ ነው።
ካናዳ ይህን ያክል ሰደትኞችን ለመቀበል ፍላጎት ያሳየችው እንደሌሎች ምእራባዊያን ሃገሮች ያስመዘገበችው ዝቀተኛ የሆነ የወሊድ ምጣኔ እና ብዛት ያላቸው ዜጎች እድሜያቸው የገፋ መሆን እንደ ምክያት ይጠቀሳል።
አሁንም ካናዳ በእድገት እንድትቀጥል ከተፈለገ ሀገሪቱ የወጭ ሃገር ዜጎችን ከመቀንስ ይልቅ መጨመር ይገባታል ተብሏል ።
በ2032 የወጭ ሃገር ዜጎች ያልተመጣጠነውን የሀገሪቱን የህዝብ ቁጥር እድገት እና የሰው ሃይል ፍላጎት ይሸፈናሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
በቡደን ሰባት ሃገራት ወስጥ ከሚገኙ ሃገራት ካናዳ ከፍተኛ የሆነ ስደተኛን ትቀበላለች።በአሃዝ ሲጠቀስ በሃገሪቱ ወስጥ ከሚገኙ ከ አራት ሰዎች መሃከል አንዱ ስደተኛ ነው ።
በካናዳ የኤም ሲ ማስተር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል መምህር የሆኑት ጎፍሪ ካሜሩን እንደ ካናዳ ያሉ በዝቅተኛ የወሊድ መጣኔ እና የዜጎች እድሜ መገፋት ፈተና የሆነባቸው ሃገራት ለስደተኞች ፈቃድ መስጠት እና ማስገባታቸው እፎየታ ይሰጣቸዋል ይላሉ ።
ወደ ካናዳ እየገቡ ሚገኙት ስደተኞ ከ ደሃ ሃራት ብቻ ሳይሆን ቀደም ብለው ወደ አሜሪካ ገበተው የነበሩ ስደተኞ አሁን ላይ የካናዳን ድንበር ጥሰው እየገቡ እንደሆነ ተሰምቷል።
ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት የሚነሳው በቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ትራምፕ የነበረው የስደተኞች ፖሊሲ አስተማማኝ ባለመሆኑ ነው ይላሉ ።
ካናዳ በዚህ አመት ብቻ ከሃያሺ አራት መቶ በላይ ስደተኞችን ተቀብላለች ። እቀዷ ግን እስከ ግማሽ ሚሊዮን ማድረስ ነው።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-22
