በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ግንቦት 29 ,1917 ከባለጸጋ ቤተሰብ ተወለዱ ። መደበኛ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁም በኋላ የተለያዩ ፖለቲካዊ ክንውኖች ውስጥ ይሳተፉ ነበር።
በ 1960ም 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ። ፕሬዝዳንት ጆን ኦፍ ኬኔዲ ። ህልማቸው ተሳክቶ አሜሪካን መምራት የጀመሩት እኚህ ሰው ሀገሪቱን እንዲመነሩ የተፈቀደላቸው ለ 3 ዐመታት ብቻ ነበር ።
ምክንያቱም በዛሬዋ ቀን ህዳር 22,1963 በዳላስ በጉብኝት ላይ ሳሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው አልፏልና ።
ነገሩ እንዲ ነው ፕሬዝዳንቱ በዳላስ ቴክሳስ በጉብኝት ላይ ናቸው ። በመሀል አስደንጋጭ ነገር ተፈጠረ ። ከየት መጣ የተባለ የጥይት እሩምታ በላያቸው ላይ ዘነበ። አብረዋቸው የነበሩ ሰወች ሊያድኗቸው የተቻላቸውን ቢያደርጉም የተነጣጠረችው ጥይት ኢላማዋን ጠብቃ ነበርና እስከወዲያኛው ሊያሸልቡ ግድ ሆነ ።
ከደቂቃዎች በኋላ ሊሀርቬ ኦስዋልድ የተባለ ግለሰብ የፕሬዝዳንቱ ገዳይ በመባል በቁጥጥር ስር ዋለ። የፕሬዝዳንቱን አሟሟት ሲመረምሩ የነበሩ ግለሰቦች ይህን ግድያ አንድ ኦስዋልድ ብቻውን በፍጹም ሊፈጽመው አይችልም ለዚህ ግድያ የሌሎች ሀገራትና የግዙፍ ድርጅቶች ሴራ መኖሩ እሙን ነው ሲሉ ሌሎች ግን ኦስዋልድ ፕሬዝዳንቱን ከሶስተኛ ፎቅ ሆኖ ባነጣጠረው ጥይት መቷቸዋል በማለት ወነጀሉ።
ምክንያታቸው ደግሞ ይህ ሰው ለሰወች ጥላቻ ያለውና ተስማምቶ መኖር የማይችል በመሆኑ ይሄን ከማድረግ ወደኋላ አይልም የሚል ነበር ።
ታዲያ በገዳይነት የተያዘው ኦስዋልድ ለምን ፈጸመከው ከጀርባህስ ማን ነበረ ተብሎ በተጠየቀበት ጊዜ ያልተጠበቀ ምላሽ ሰጠ
“እየሆነ ስላለው ነገር የማውቀው ነገር የለም እኔ በፍጹም የፕሬዝድንቱ ገዳይ አይደለሁም ስለሳቸውም የሰማሁት ከጋዜጠኞች ነው።” በማለት።
ነገሩን ይበልጥ ውስብስብ የሚያደርገው ደግሞ ይህ ሰው አልገደልኩም ሲል ቃሉን በሰጠ በሁለትኛው ቀን ተገድሎ መገኘቱ ነው።
አሁን የኬኔዲ ገዳይ ኦስዋልድ ብቻ እንዳልሆነ መርማሪዎች ማመን ጀመሩ ምን አልባትም እዚህ ግድያ ውስጥ የቺካጎ የማፊያ ቡድን እጅ ሊኖር ይችላል የሚል ጥርጣሬ ሲኖር በሌላ በኩል ደግሞ ሶፌት ህብረት ግድያውን ፈጽማለች የሚሉም ነበሩ።
ነገር ግን በ ፕሬዝዳንቱ ሞት የተለያዩ ተጠርጣሪ ድርጅቶች እጅ ቢቀሰርባቸውም ፤ የዚያ የ 24 ዓመት አፍላ ወጣት ግድያ መረጃዎችን ሁሉ አዳፍኖት ነበርና ምንም አይሳነኝም ባይዋ አሜሪካ ዛሬም ድረስ የፕሬዝዳንቴ ገዳይ ይህ ነው ማለት ተስኗት ነገሩ እንደተዳፈነ ዝምታን መርጣለች ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-11-22
