ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ በፕሪቶሪያ የተፈረመው ስምምነት በአስቸኳይ እንዲተገበር ጠየቀች

አሜሪካ በፊደራል መንግስትና በህወሃት መካከል የተፈረመው ስምምነት በአስቸኳይ ወደ ተግባር እንዲገባ ጠየቀች ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ዙሪያ በስልክ ተነጋገረዋል።

ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለማድረስና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበረበት ለመመለስ እየሠራ ላለው ሥራም ዕውቅና ሰጥተዋል ።

የውጭ ኃይሎች መውጣትና የትግራይ ኃይሎች ትጥቅ መፍታትን በፍጥነት ተግባራዊ የማድረግ ሂደትም ሊፋጠን እንደሚገባ አንቶንዮ ብሊንከን ጥሪ አቅርበዋል።

አሜሪካ ለሰላም ስምምነቱ መተግበር አስፈላጊውን ትብብር እንደምታደርግ እና በአፍሪካ ኅብረት በኩል የተጀመረውን ሂደት እንደምትደግፍም ከጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ጋር በነበራቸው ቆይታ መናገራቸውን ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-11-23