ሀገሬ ቲቪ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ500 ሚሊዮን ብር የኢንቨስትመንት ስምምነት አካሄደ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ500 ሚሊዮን ብር የኢንቨስትመንት ስምምነት ፓሮን ትሬዲንግ ከተሰኘው ሀገር በቀል ድርጅት ጋር አካሄደ ።

ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ እና የፓሮን ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ አስሬ ተፈራርመዋል።

ድርጅቱ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ሲሆን በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ 500 ሚሊዮን ብር ሀብት ፈሰስ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ።

በስምምነቱ መሰረት ፓሮን ትሬዲንግ ሁለት ሄክታር የለማ መሬት የተረከበ ሲሆን ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-23