
ማላዊ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሰማኒያ ስምንት ሚሊየን ዶላር ብድር አገኘች። ብድሩ በዋናነት ሃገሪቱ የገጠማትን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ያለመ ነው ተብሏል።
የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ክፉኛ በምግብ እጥረት ተፈተነዋል ካላቸው 48 ሃገራት ወስጥ ማላዊ አንዷ ሰትሆን ተቋሙ ለአባል ሃገራቱ በአስቸኳይ የምግብ ደጋፍ እና ፣ከፍትኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ፈተና ለሆነባቸው ሃገራት ብድር እፈቅዳለሁ ብሏል ።
የአለም አቀፉ የገዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክቶር እንዳሉት የማላዊ ባለስልጣናት በፍጥነት ከእዳ ጭንቀት በማወጣት የደጋፉ ተደራሽነት ላይ ሊሰሩ ይገባቸዋል ብለዋል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-23