
የካሜሮን ህዝብ 68 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ተዘረፈ። የካሜሮን የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባሳለፍነው የአውሮፓዊያኑ 2021 የካሜሮን ህዝብ 68 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በሙስና ተሰርቋል ብሏል።
ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በቀረበዉ ሪፖርት መሰረት በሀሰተኛ ፊርማ ፣ በሀሰተኛ የመሬት ይዞታዎች ፣ ወድ ዩኒቨርስቲዎች ለመግባት ጉቦ በመስጠት እና በአንዳንድ የህዝብ ሆስፒታሎች ውስጥ ካሉ ታማሚዎች ገንዘብ በመዝረፍ ነው የሙስና ወንጀሉ የተፈጸመው፡፡
የኮሚሽኑን ሪፖርት ተከትሎ 500 ያህል ሰዎች ከስራ የተባረሩ ሲሆን 37 ሰዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በማህሌት አማረ
2022-11-23