ሀገሬ ቲቪ

“በሰዓት 5 ሴቶች በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ” የተባበሩት መንግስታት

ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት 2021 45 ሺሕ ሴቶች በገዛ ቤተሰባቸው አልያም በቅርብ ቤተሰባቸው መገደላቸውን ሪፖርት አመላከተ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት እንዳለው በመላው ዓለም ከሚገኙ ሴቶች ውስጥ በሰዓት5 ሴቶች በቅርብ የቤተሰባቸው አባል ወይም በገዛ ቤተሰባቸው ይገደላሉ።

ይህ በቤተሰብ ውስጥ ያለው ብቻ ተተንቶ እንጂ ቁጥሩ የበለጠ ሊጨምር የሚችል መሆኑን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጿል። በሴቶች ላይ ግድያ ከሚፈፀምባቸው አህጉሮች ኤዢያ ቀዳሚዋ ስትሆን አፍሪካ በሁለተኝነት ተቀምጣለች።

በሳምሶን ገድሉ
2022-11-24