ሀገሬ ቲቪ

የቻይና በኮቪድ የሚያዙ ሰዎች ዳግም ጨመረ

ቻይና ኮቪድ 19 ከተከሰተ ጀምሮ ያልተመዘገበ አዲስ የመያዝ ቁጥር መመዝገቡን ይፋ አደረገች። ሀገሪቱ በአንድ ቀን ብቻ 31,527 ዜጎቼ በቫይረሱ ተይዘዋል ብላለች።

ቁጥሩ በ2014 ዓ.ም. ሚያዚያ ወር በአንድ ቀን 28 ሺሕ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ይፋ ካደረገች በኋላ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

በያዝነው ወር በኮቪድ ሳቢያ ለሞት የተዳረገ ሰው በመገኘቱ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ላላ ብሎ የነበረውን ዕቀባ በተወሰነ መንገድ ዳግም ተግባራዊ አድርገዋል።

በቤጂንግ ሱቆች፣ ትምህርት ቤቶች እና ሬስቶራንቶች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ሲደረግ፤ 6 ሚሊዮን የሚኖርባትን ዠንግዡ ደግሞ ከእንቅስቃሴ መታገዷን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-11-24