የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2027 25 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገለጸ ።
ለዚህም የበረራ መዳረሻውንና የአውሮፕላን ቁጥሩን በእጥፍ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
65 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን እና 3 ሚሊዮን ቶን ጭነት የማጓጓዝ አቅም እንዲኖረው እንቅስቃሴ መጀመሩም ተገልጿል ።
ይሄንን ዕቅዱን ለማሳካት አውሮፕላኖቹን ወደ 271 ለማሳደግ እየሰራ ስለመሆኑም ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-11-24
