ሀገሬ ቲቪ

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደንብና መመሪያ አክብረው እንዲሠሩ ጥሪ ቀረበ

ተቋማቱ ብቃት ያላቸውን ዜጎች ማፍራት እንዲችሉ መንግሥት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየደገፋቸው መሆኑን የትምህርት ሚንስቴር አስታውቋል።

ተገልጋይ ዜጎችም በተቋማቱ ውስጥ ለመማር ከመመዝገባቸው በፊት የብቃት ማረጋገጫዎችን ማረጋገጥ እንዳለባቸውም ተጠቁሟል።

ማህበረሰቡ ህግን አክብረው የሚሰሩትን በመደገፍ ከህግ ውጭ የሚንቀሳቀሱትን በማጋለጥ እንዲተባበር ትምህርት ሚንስቴር ጥሪ አቅርቧል። መረጃውን ከትምህርት ሚንስተር የማህበራዊ ትስስር ገፅ አግኝተነዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-11-24