ሀገሬ ቲቪ

የጨመረው የህንድ እና ሩስያ የነዳጅ ግብይት

በነዳጅ ፍጆታ ከአለም ሶስተኛ የሆነችው ህንድ ከሩስያ የምትገዛው የድፍድፍ ነዳጅ መጠን ከፍ ብሏል ተባለ። ህንድ 80 በመቶ የነዳጅ ፍጆታዋን ከውጭ በማስገባት ታሟላለች። በ2021 ህንድ ከሩስያ ያስገባችው የነዳጅ መጠን 12 ሚሊዮን በርሜል የነበረ ሲሆን አሁን ግን በአራት ወራት ብቻ 26 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ከሞስኮ የማስገባት ስምምነት ላይ ደርሳለች። ሃገራቱ ለግብይታቸው ሩብልን እየተጠቀሙ ነው።

በሀገሬ ቲቪ
2022-04-27