ሀገሬ ቲቪ

የነዋሪነት መታወቂያ እድሳት አገልግሎት ላይ የተነሱ ቅሬታዎች

በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለ4ወራት ተቋርጦ የነበረው የነዋሪነት መታወቂያ እድሳት አገልግሎት ከህዳር 1 ቀን 2015 ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መሰጠት ተጀምሯል።

እኛም አገልግሎት አሰጣጡ ምን ይመስላል የሚለውን ለመቃኘት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ተገኝተን ነበር። በጉዳዩ ላይ ያናገርናቸው ተገልጋዮች አገልግሎቱን ለማግኘት ረጅም ሰዓት የመሰለፍ፣ በፍጥነት ያለመስተናገድ እና መሠል ችግሮች እንዳማረራቸው ነግረውናል።

እኛም የተገልጋዮችን ቅሬታ እና ጥያቄ ለየካ ከ/ከተማ ወረዳ 05 የወሳኝ ኩነት ጽ/ቤት ኃላፊ የኾኑት ወ/ሮ መቅደስ ቱፋ አቅርበናል። ቅሬታውን እንደሚቀበሉት ተናግረው የሲስተም መጨናነቅ በቀን ከ 70 በላይ ተገልጋዮችን እንዳናስተናግድ አድርጎናል ብለዋል በዚህም ምክን ያት በርካታ ሰዎች ረዥም ሰዐት እንዲጠብቁ ኾነዋል።

አሁንም ቢኾን ተገልጋዩ ሳይንገላታ እንዲስተናገድ የተነሱ ቅሬታዎን እንደሚፈታ ለየካ ከ/ከተማ ወረዳ 05 የወሳኝ ኩነት ጽ/ቤት ኃላፊ የኾኑት ወ/ሮ መቅደስ ቱፋ ተናገዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-25