በአፍሪካ የልማት አጋርነት (ኔፓድ) የአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጄንሲ ኢትዮጵያን በፈጠራ እና በስራ ዕድል ዘርፍ የማገዝ ፍላጎቱን ገለጸ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ከአዩዳ ኔፓድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናርዶስ በቀለ ጋር በኒጀር ኒያሚ ተወያያተዋል።
የአህጉራዊ ተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናርዶስ በቀለ ኢትዮጵያ በልማቱ ዘርፍ የምታደርገውን እንቅስቃሴ መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በኒጄር ከ17ተኛው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ጉባኤ ጎን ለጎን ውይይቱ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በስንዴ ምርት ላይ ብሎም በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሙዚየም ን ጨምሮ በግብርና እና ቴክኖሎጂ ላይ የሚያተኩር ውይይት ለማድረግ ተስማምተዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-11-25
