
የቢል ጌትስ ፋውንዴሽን ለአፍሪካ የ7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ እንደሆነ ገለጸ። ፋውንዴሽኑ በቀጣዮቹ አራት ዓመታት ይሄንን ድጋፍ ለአፍሪካ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ቢል ጌትስ የዩክሬይን ጦርነት ለአፍሪካ የሚደረገውን ድጋፍ አስተጓጉሎታል ብለዋል።
የሰባት ቢሊዮን ዶላር ድጋፉ ቀደም ካሉት አራት ዓመታት በ40 በመቶ ያደገ ሲሆን ረሃብን፣ በሽታ እና ድህነትን ለመቀነስ እንዲሁም የጾታ እኩልነትን ለመፍጠር ይውላል ተብሏል።
በብሩክ ያሬድ
2022-11-25