ሀገሬ ቲቪ

ጋና የነዳጅ ዘይትን በወርቅ ልትገዛ ነው

ጋና የነዳጅ ዘይትን ለመግዛት ዶላርን መጠቀም ላቆም ነው ብላለች። ለግብይቱ ከዶላር ይልቅ ወርቅን እንደ ክፍያ እንደምትጠቀም የሀገሪቱ መንግስት ይፋ አድርጓል።

ይህም ሀገሪቷ አጋጥሞኛል ላለችው የምንዛሬ እጥረት ዶላርን በካዝናዋ ለመቆጠብ የተደረገ እርምጃ መሆኑን ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሙሀመዱ ቧዉሚያ ተናግረዋል።

ጋና በጥር ወር 2009 ዓ.ም. የተጣራ የነዳጅ ዘይት ማምረቻዋ ከፈነዳ በኋላ ድፍድፉን የነዳጅ ዘይት ወደ ውጪ በመላክ የተጣራውን ወደ ሀገሯ ታስገባለች። ይህም ለሀገሪቷ ከፍተኛ የውች ምንዛሪ እንድታወጣ ሲያደርጋት መቆየቱ አልጄዚራ ዘግቧል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-11-25