የሰላም ሚኒስቴር ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመኾን የኢትዮጵያ የሰላም ም/ቤትን በዛሬው ዕለት መስርቷል።
ይህ የሰላም ም/ቤት የጋራ ዕቅድ እና ሀሳብ የኾነውን ሰላም በጋራ ለማስፈን ምቹ ኹኔታን የሚፈጥር እንደኾነ በመድረኩ ተነስቷል።
ይህ ምክር ቤት ስለ ሰላም ዋጋ ከግለሰብ ጀምሮ ግንዛቤ መፍጠር፣ በማህበረሰብ ደረጃ በሰለጠነ መንገድ አለመግባብትን የመፍታት ባሕል ማሳደግ እና አጠቃላይ የሰላም ግባታን ዘላቂ ማድረግ የሚሉ ሶስት ዋና ግቦች እንዳሉት ነው የሰላም ሚንስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የተናገሩት።
በሀገሪቱ የሚታዩትን አለመግባባቶች እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል።
ዛሬ የተመሠረተው የሰላም ም/ቤት ታዲያ ከአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ምን ይለየዋል ስንል ጠይቀናል።ኮሚሽኑ በጊዜ ገደብ የተቀመጠ የሚያሳካው ዓላማ ሲኖረው ም/ቤቱ ግን የማይቋረጥ የሠላም ግንባታ ላይ የሚያተኩር እንደኾነ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-28
