ሀገሬ ቲቪ

የምዕራባውያን የሩሲያ ነዳጅ ዋጋ መቁረጥ

ከሩሲያ ነዳጅ ዘይት ላይ ያላቸውን ጥገኝነት መቀነስ ለሚፈልጉት ምዕራባውያን ያሰቡት ሁሉ እየሆነላቸው አይመስልም።

ከሳምንታት በፊት በኢንዶኔዢያዋ ባሊ ለዓመታዊ ስብሰባቸው የተቀመጡት ሀያላን ሀገራት በሩሲያ የነዳጅ ዘይት ላይ የመግዣ ዋጋ ለመቁረጥ ተስማምተው ተለያይተዋል። ነገሩ መስማማት ብቻ ሆነ እንጂ።

ሩሲያ ለአውሮፓውያኑ ታቀርብ የነበረውን ጋዝ ሙሉ በሙሉ አቋርጣለች እና ነው። በዚህ ውስጥ የነዳጅ መግዣ ዋጋችን ስንት ይሁን በሚለው ላይ ሀገራቱ ከመስማማት ይልቅ ተከፋፍለው ቀነገደባቸው ተቃርቦባቸዋል።

ሀገራቱ የተፈጥሮ ጋዙን በበርሜል 65 እስከ 70 ዶላር ብቻ መግዛት አለባቸው የአውሮፓ ህብረት ሀሳብ ነው። ሀገራቱ ግን እንዴት ተደርጎ ሲሆን ሲሆን ከ50 ዶላር በታች ማድረግ ይገባል ባይ ናቸው።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ዋጋው ከ20 እስከ 50 ባለው ውስጥ መቀመጥ አለበት ሲሉ ይሞግታሉ።

እኛ የሩሲያ ትልቁ የቢዝነስ አጋር ነን የሚሉት የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሮሱላ ቮን ደር ሌይን ያ ትላንት ነው፤ ዛሬ ላይ ግን ከሩሲያ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማቋረጥ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው ባይ ናቸው።

“የነዳጅ ጉዳይ አስቸጋሪ የሚሆነው ወደብ አልባ ለሆኑት ሀገራት ነው። የዳጁን በባህር ሊያስገቡ አይችሉም ሌላ አማራጭ መንገዶች ያስፈልጋሉ። ነገሩ የሳምንታት ግዜ ቢወስድ ነው። እርምጃውን መውሰዳችን አይቀርም።”

ወዲህ ነገሩ የተገላቢጦሽ ይመስላል የሩሲያ የጋዝ ምርቶች የሚሸጡበት አሁናዊ ዋጋ በበርሜል 52 ዶላር ብቻ ነው። ይህ የምዕራባውያኑ ውሳኔ ሩሲያን አይደለም ኢኮኖሚዋን ሊያዳክመው ቀርቶ በጥቂቱም ቢሆን አላፋዘዘውም።

ታዲያ አውሮፓውያኑ ፊታቸውን ያዞሩባት ሩሲያ ከህንድ እና ቻይና ጋር የነዳጅ ገበያውን አድርታዋለች። ከዓለም አቀፍ ዋጋ ዝቅ በማድረግ የተፈጥሮ ሀብቷን እየሸጠችው ትገኛለች።ያውም በሩብል።

ሁለተኛዋ የሩሲያ ትልቋ የነዳጅ ሸማች ሀገር የሆነችው ህንድ ከሁለት ወራት በፊት የተመዘገበው መረጃ እንደሚያመላክተው ወደ ሀገሯ ያስገባችው የሩሲያ የነዳጅ ዘይት ምርት በወሩ በ23 በመቶ ጨምሯል።

ለዚያም ይመስላል የህንዱ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጃይሻንካር የሩሲያውን አቻቸውን ሰርጌ ላቭሮቭን ባገኙበት ሰዓት ሩሲያ በግዜው ውስጥ ተፈትና የተረጋገጠች አጋራችን ናት ማለታቸው።

በሌላኛው ጥግ ያለችው ቻይናም ብትሆን የሩሲያን ነዳጅ አብዝታ ወደ ሀገሯ የምታስገባ ቁጥር 1 ሀገር ናት። በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት መጀመር ማግስት 37.5 ቢሊዮን ዶላር የተፈጥሮ ጋዝ ስምምነትን ፈርማለች ያውም ክፍያውን በሩሲያ የመገበያያ ገንዘብ ሩብል ለመክፈል።

ወዲህ የኃይል እጥረት እና መጣው መጣው የሚለው የበረዶ ክረምት፤ ወዲያ ያመረረ የሩሲያን ኢኮኖሚ የማዳከም ፍላጎት ከሩሲያ ጥገኝነት መላቀቅ ለተሳናቸው አውሮፓውያን ፈተናው ከፊታቸው ተደቅኗል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-11-28