በአለም የእግር ኳስ ታሪክ ወስጥ ስሙን በደማቁ ያጻፈ ተጫዋች ነው። በዙዎች አይረሱትም ፣ በኳስ ይዝናናል ፣ ደጋፊን ያዝናናል፤ ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሬራ ።
የተወለደው በብራዚል በፖርቶ አልግሪ በተባለ መንደር መጋቢት 19፣ 1980 ዓ.ም ነው ።እንደማንኛውም በራዚላዊ ህጻናት በበራዚል ጎዳናዎች ኳስን ሲያንከባለል የተመለከተው አባት በአቅራቢያው በሚገኝ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አስገባው ።
በተከለ ሰወነት ትንሽ የነበረው ሮናልዲንሆ በጫወታ ወቅት የቡድን አጋሮችሁን ከጉልበት ይልቅ በእግርኳስ ቴክኒክ ጎልን ያስቆጠርባቸው ነበር ። በሮናሊዲንሆን በአንድ አጋጣሚ በአከባቢው ለሚገኝ አንድ ክለብ ተጫወቶ ቡድኑ 23 ለዜሮ ሲያሸንፍ የሁሉም ጎል አስቆጣሪ የ 13 አመቱ ሮናልዲሆ ነበር ።
ከዚ በኋላ ነበር ታዲያ ትንሹ ብራዚላዊ በተለያዩ የብራዚል ክለቦች ቀለብን መሳብ የጀመረው። ከጥቂት አመታት በኋላ በክለብ እግርኳስ የመጅመሪያው የነበርው የብራዚል ከለብ ግሬሚዮን ተቀላቀለ።
ግሬሚዮን በተቀላቀለ በአመቱ በ 47 ጫወታ 20 ጎሎችን ማሰቆጠር ቻለ። በግሪሜዮ የተሳካ አመትን ያስለፈው ሮናልድኒንሆ ዲያሲሲ ሞሬራ በተለያዩ የአወሮፓ ክለቦች እይታ ወስጥ መገባት ቻለ ።
በ2001 የፈረንሳዩ ፓሪሰን ጀርመን በአምስት አመት ኮንትራት ብራዚሊያዊወን ተሰፈኛ በ 5 ሚሊየን ዩሮ አስፈረመው ። በፈረንሳዩ ክለብ የተቀላለው ሮናልዲንሆ በፍሬንች ሊግ በከለቡ ቋሚ ተሰላፊ ሆኖ መጫወት እድል ባያገኝም ተቀየሮ በመግባት ጎል ማስቆጠር ጀመረ ።
ሮናልዲንሆ ፓርሰንት ጀርመን በተቀላቀለቅበት አመት ለክለቡ በወሳኝ ጫወታዎች ላይ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። በፈርንሳይ ፓሪስ በሁለት አመት ቆይታ በ 55 ጫዎታዎች 17 ግቦችን ያስቆጠረውን ሮናልዲሆን ለማስኮበለል ታላላቅ የአወሮፓ ክለቦች ፍክክር ወስጥ ገቡ።
የእንግሊዙ ማስችስተር ዩናይትድ እስከ መጨርሻው ሰአት ድረስ ማሰፈርም እድል ቢኖረው በካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ተነጠቀ ። ባርሳ ሮናልዲንሆ ጎቾ 30 ሚሊየን ዩሮ የግሉ ማደርግ ቻለ ።
የወቅቱ የክለቡ አሰልጣኝ የነበረው ፍራንክ ራይካርድ ሰለ ሮናዲሆ ሲናገር ኳስ በእሱ እግር ስትገባ የተለየች ናት ይላል። ሮናዲንሆ በባርሳ ማሊያ የመጀመሪያወን ጎል ያስቆጠረው ከሲቪያ ጋር በነበረ የላሊጋ ጫወታ ነበር ።
ከዚህ በኋላ ነበር እግር ኳስ አለም ሰሙን መገንባት የጀመረው ። በ2004/2005 የውድድር አመት በፊፋ የአለም ምርጥ ተጫዋች ተበሎ ተመርጧል ።
የሰኬት አመታትን በባርሳ ያስለፈው እና በአዝናኝ እና በቂንጠኛ የኳስ ክህሎቱ ደጋፊን የሚያዘናናው ተጫዋች የምንም ጊዜ ተቀናቃኛቸውን ሪያልማድሪድን ሳይቀር በኤልክላሲኮ ጫወታ ላይ አስጨብጨቧቸዋል ።
በ2005/2006 በክልበ ስኬት የተሻለ አመትን ያስለፈው ሮናልዲሆን ዲያሲስ ሞሬራ በፌፋ ለሁለትኛ ግዜ ምርጥ ተጫዋች ተበሎ ተመረጠ ። በዚህ በቻ ያላበቃው ሮናልዲንሆ በዛሬው ቀን ከ17 አመት በፊት የአለም መርጡ ተጫዋች በመባል የባሎንዶር ሽልማትን አገኘ ።
ተጫዋችሁ ከዚህ በላይ ክብሮችን ማሸንፍ የሚችል ቢሆንም ከእግር ኳስ ህይወቱ ውጭ አብዛኝው ብራዚሊያዊያኖች በሚታሙበት ዳንኪራ እና የመሸታ ቤት ወሎ ሮናልዲሆም ተሰታፊ ነበር ። የእግር ኳስ ህይወቱም በአጨሩ የተቀጨው በዚሁ መክንያት ነበር ።
በእግር ኳስ ህይወቱ መጨርሻ የባልዶር ከብረን ከተቀዳጀንበት ባርሳ በመልቀቀ በጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ፣ በብራዚሉ ፈላሚንጎ ፣ በአተሌቲኮ ሚኒየሮ ፣ በኩሬታሮ በመጨረሻም በፉሉሚናሴ ከተጫወተ በኋላ እግር ኳስን በ37 አመቱ በ2018 በይፋ ከ እግር ኳስ እራሱን አግልሏል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-28
