የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ መንግስት ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ያለገደብ ተደራሽ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሺፈራው ተክለማርያም ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ወደትግራይ ክልል 32 ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል እና ከ360 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተደራሽ መደረጉንም ገለጸዋል።
እርዳታው በየብስ በአራት ኮሪደሮች በተጨማሪም በመቀሌ እና ሽሬ አውሮፕላን ማረፊያውች እየደረሰ መሆኑንም ተናግረዋል።
መንግስት ከፍተኛ መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ፣ ለአካባቢው ነዋሪ የውሃና ለንጽህና መጠበቂያ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ተደራሽ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በአብርሃም በለጠ
2022-11-28
