
የኬንያ መሰረት ያለው እና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የሚሰጠው ኤም ሽዋሪ በሀገራችን አገልግሎቱን ለመጀመር የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያጠናክር ገለጸ።
ኤንሲቢኤ ግሩፕ ስለዚህ አገልግሎቱ እንደገለጸው አገልግሎቱን በጋና፣ ኮንጎ እና ኢትዮጵያ ለማስፋት ከሀገራቱ የባንክ እና ቴሌኮም ተቋማት ጋር እየመከረ መሆኑን ጠቁሟል።
ለዚህም ከቀጠናው ባንኮች ጋር ያለውን አጋርነት ለማጠንከር እየሰራ ሲሆን በተለይም በኢትዮጵያ እና ኮንጎ ያለው የህዝብ ቁጥር እና ያልተነካው የባንክ ዘርፉ እንደሳበው ገልጿል።
ተቋሙ በታንዛንያ፣ ኡጋንዳ እና ርዋንዳ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስታውሶ የዘገበው ቢዝነስደይሊ አፍሪካ ነው።
በአብርሃም በለጠ
2022-11-28