
የ80 ዓመቱ ፕሬዝዳንት እና ለ43 ዓመታት ኢኳተርያል ጊኒን የመሩት ቲዎዶር ኦብያንግ ለስድስተኛ ጊዜ እንደገና ተመረጡ።
ከ1970ዎቹ መጀመሪያ ጀመሮ በሀገሪቱ በስልጣን ላይ የቆዩት ኦብያንግ በአሁኑ ምርጫ የሀገሪቱ የቀጣይ ሰባት ዓመታትም ፕሬዝዳንት እርሳቸው መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ኦብያንግ 95 በመቶ በሚጠጋ ውጤት ለሀገሪቱ ፕሪዝዳንትነት፣ ለስድስተኛ ጊዜ መመረጣቸውን የጊኒ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።
በሀገሪቱ ምርጫ ከመጀመሩ አስቀድሞ ሁከትን ለመከላከል በሚል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ከመታሰራቸውም በተጨማሪ ሀገሪቱ ከምርጫ ቅስቀሳው በፊትም ከጎረቤቶቿ ጋቦን እና ካሜሮን የነበራትን ድንበር ዘግታለች።
በአብርሃም በለጠ
2022-11-28