ቻይና እየተከተለችው ያለውን የዜሮ ኮቪድ ፖሊሲ በተወሰነ መንገድ ካላላች ከቀናት በኋላ በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በኮቪድ ተያዘ።
በአንድ ቀን ብቻ 40 ሺህ 52 ሰው የተያዘ ሲሆን፣ ከነዚህም 36 ሺህ 304 ያክሉ ምልክቱን ማሳየት መጀመራቸውን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል።
ይሄኛው ማዕበል የቻይናን የጤና ስርዓት እና የምትወስደው ርምጃ ላይ ጫና ሊያሳድር እንደሚችልም ተጠቁሟል። በቀጣዮቹ ሳምንታትም ከፍ ያለ የሞት መጠን በቻይና ሊመዘገብ እንደሚችል ተገልጿል።
በአብርሃም በለጠ
2022-11-28
